በቦሌ በሻሌ ኮንዶሚኒየም ከ6 ሺህ በላይ አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን በቦሌ በሻሌ 40/60 ኮንዶሚኒየም የሚገኙ ከ6 ሺህ በላይ አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ነዋሪዎቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ከአራብሳ ሃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዝርጋታ ያከናወነ ሲሆን 6.7 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታና 3 ባለ 800 ኪቮአ፣ 12 ባለ 630 ኪቮአ፣ 30 ባለ 1250 ኪቮአ በአጠቃላይ 45 ትራንስፎርመር ተከላ አከናውኗል፡፡

ነዋሪዎቹ ካሁን በፊት ባለ ሶስት ፌዝ ቆጣሪ በጋራ ይጠቀሙ የነበረ ሲሆን በዚህም በኃይል እጥረትና በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ሲቸገሩ ቆይተዋል፡፡በአሁኑ ሰዓት በተከናወነው የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ዝርጋታ ለእያንዳንዳቸው ቆጣሪ ተገጥሞላቸው ያልተቆራረጠ ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል፡፡

ሪጅኑ ባከናወነው የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ዝርጋታ በበሻሌ ኮንዶሚኒየም ነዋሪ የሆኑ 6700 አባወራዎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆነዋል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃውን አድርሱናል ፡፡

የካቲት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *