የፋይዳ መታወቂያን ለመያዝ የንግዱ ማህበረሰብ ስጋት ሊገባው አይገባም ተብሏል፡፡
ይህንን ያሉት የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ ናቸው።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ባለቤት መሆን በተለይ የንግዱን ማህበረሰብ ስጋት ውስጥ የሚጥለው ሊሆን አይገባም ያሉት አቶ ዮዳሄ፣መንግስት በተለየ ሁኔታ ዜጎቹን የሚያድንበት ወይንም የሚከታተልበት ስርዓት እንዳልሆነ አስታውቀዋል።
አንድ አካል ብቻ ተጠያቂ እንዲሆን የሚያደርግ ስርዓት መኖር የለበትም ያሉት አቶ ዮዳሄ መንግስትም አጥፊ ሆኖ ሲገኝ ተጠያቂ የሚሆንበት ስርዓትም እንዳለ አንስተዋል።
ህብረተሰቡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ስጋት ለኖረው እንደማይገባ እና የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዙ ምንም አይነት አሉታዊ ጉዳትን እንደማያደርስበት ተናግረዋል፡፡
አንድ ሰው የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ሲሆን በአብኛዛው ማንነቱን ገላጭ የሆኑ መረጃዎቹን በዚህ ስርዓት ውስጥ እንደማይካተቱ እና ይህም የግለሰቡን ሚስጥራዊ መረጃዎች ለመጠበቅ እንደሚረዳ ነው የገለፁት፡፡
በአሁኑ ሰዓት 37.5 ሰው የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ያገኘሲሆን እስከ መጪው ግንቦት ወር 2018 ዓ/ም ድረስ እንደ ሀገር 90 ሚሊዮን ሰዎችን የመመዝገብ እቅድ ተይዟል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
መጋቢት 01/2018 ዓ.ም
