በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ከ1 ሺህ 4መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 4መቶ67 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸዉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
‎
‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 5 ዙር በረራ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 15 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
‎
‎መስከረም 5/2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 60 ሺህ 5መቶ19 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎ሚኒስቴሩ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ የፍልሰት አማራጭን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡
‎
‎በተጨማሪም ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብሏል።

መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *