የቶንሲል ህክምና አለማድረግ በከፍተኛ መጠን ለልብ ህመም ተጋላጭ እያደረገ ስለመምጣቱ ተገለፀ

በኢትዮጵያ ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ ባይቻልም በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የልብ ታማሚ ስለመኖሩ ሰምተናል።

በኢትዮጵያ ብቸኛ የልብ ማዕከል የሆነዉ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በአመት 3መቶ ሺህ የሚጠጋ አዲስ የልብ ህመም ታካሚዎች እየተቀበለ መሆኑ ተገልጿል።

የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልኤዘር ሀይሌ፤ ይህ ከቶንሲል ህመም ጋር ተያይዞ የመጣዉ የልብ ህመም ተጋላጭነት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ለህመሙ የሚደረጉ ህክምናዎች ላይ መዘናጋቶች ስለሚታዩ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዶ/ር ኤልኤዘር እንደገለፁት፤”የቶንሲል ህመም ህክምናን በተገቢዉ መልኩ፣በተገቢዉ ቀን እንዲሁም ትክክለኛዉን ዶዝ ባለማግኘት ወይም ህመሙ ሳይታከም በመቅረቱ ሮማቲክ ኸርት ዲዚዝ እየታየ ይገኛል” ብለዋል።

ለዚህ መሰሉ የልብ ህመም ተጋላጭ የሆኑ ታማሚዎችን ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ባይቻልም በዚህ ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የልብ ታካሚዎች እንዳሉ አያይዘዉ ገልፀዋል።

በዚህ የልብ ህመም ሳቢያ በየዓመቱ ከ2መቶ88 ሺህ በላይ ሰዎች ለሞት የሚዳረጉ ሲሆን፤ እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ ይህ የልብ በሽታ በአብዛኛው ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ያሉ ሰዎች ላይ ሊታይ እንደሚችልም መረጃዎች ጠቁመዋል።

ለዓመታት ቀዶ ሕክምና እና የተለያዩ የልብ ሕክምናዎችን እየሰጠ ባለዉ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በሺዎች የሚቆጠሩ ሕጻናት ሕክምናውን ለማግኘት አሁንም ወረፋ እየተጠባበቁ እንዳሉ ተነግሯል።

ቁምነገር አየለ

መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *