አልቱራ የተሰኘች የቱርክ የነዳጅ ጫኝ መርከብ በኢስታንቡል ቦስፎረስ ወሽመጥ አቅራቢያ በድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባት ተዘገበ።
የቱርኩ ኤን ቲቪ ጣቢያ እንደገለጸው፤ጥቃቱ የደረሰው መርከቧ ከቦስፎረስ ወሽመጥ 28 ኪሎ ሜትር ያህል ርቀት ላይ እያለች ነው።
ጥቃቱን ተከትሎ በመርከቧ ላይ የነበሩ 27 ሰራተኞች በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑንና ምንም ዓይነት የህይወት መጥፋት እንዳልደረሰ ዘገባው አመልክቷል።
ስለ ጥቃቱ መንስኤም ሆነ ከጀርባው ስላለው አካል እስካሁን በዝርዝር የተገለጸ ነገር የለም።
ልዑል ወልዴ
መጋቢት 17/2018 ዓ.ም
