ይህ የፈጠራ ውጤት ከተለመዱትና ከአካል ጋር ከሚጣበቁ የኃይል ልብሶች በተለየ መልኩ፤ ከለባሹ ጀርባ እንደ ተጨማሪ ጥንድ እግር በመሆን አብሮ የሚራመድ ሲሆን፤ እስከ 20 ኪሎ ግራም የሚደርስ ሸክምን ሙሉ በሙሉ ተሸክሞ የመጓዝ አቅም አለው።
መሣሪያው ለባሹ ወደ ፊት እንዲገፋ የሚያስፈልገውን ሜካኒካዊ ኃይል በራሱ ስለሚያመነጭ በእግር ጉዞ ወቅት የሚባክነውን የሰውነት ጉልበት እስከ 35 በመቶ በመቀነስ ረገድ ከሌሎች መሰል ቴክኖሎጂዎች የላቀ ውጤት አስመዝግቧል።
ይህ የቴክኖሎጂ ውጤት የሰውን የመምራት ብቃት እና የሮቦትን የከባድ ስራ አቅም ለማቀናጀት ያለመ ቢሆንም፤በማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ ግን ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል።
ብዙዎች ለባሹ ድንገት ቢወድቅ የሮቦቱ ክብደት አከርካሪው ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ሐመረ ፍሬዉ
መጋቢት 18/2018 ዓ.ም
