ሀገራችን የበሽታው ከፍተኛ ጫና ካለባቸው 30 የዓለም ሀገራት ውስጥም አንዷ መሆኗ ተገልጿል።
ይህ የተገለጸው የዓለም የቲቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ በጤናው ዘርፍና በሚዲያ ባለሙያዎች መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሚዲያ ፎረም ላይ ነው።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ህይወት ሠለሞን እንደገለጹት፤ መንግሥት ለአንድ የቲቢ ታካሚ በዓመት ከ6 እስከ 8 ሺህ ዶላር ወጪ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
የቲቢ መድኃኒት ለታማሚዎች በነፃ ነው የሚሰጠው ከዚህ ውጭ መድኃኒቱን ከፍሎ የሚወስድ ሰው ካለ እየገዛ ያለው ‹‹የተሰረቀ መድኃኒት›› ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በአሁኑ ወቅት ከ2 ሺህ በላይ የግል ጤና ተቋማት ምርመራና ሕክምና እየሰጡ ሲሆን ለ1ሺህ ተቋማት መመርመሪያ መሣሪያዎች መሰራጨታቸውን ገልጸዋል።
በገጠሩ አካባቢ ለሚገኙ 6መቶ90 ላቦራቶሪዎች የሶላር ፓነል ዝርጋታ መከናወኑንም አመልክተዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
መጋቢት 18/2018 ዓ.ም
