ከ2015-2017 በጀት ዓመት 17 የሚሆኑ ተቋማት በህገወጥ መንገድ የጀነቲክ ሀብት ዝውውር ማድረጋቸው ተገለጸ

ይህ የተገለጸዉ በኢትዮጵያ ብዝሀ ህይወት ኢንስቲትዩት የጄኔቲክ ሀብትና የማሕበረሰብ ዕውቀት አርክቦት አተገባበር ዙርያ የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ባካሄደው ምርመራ ነዉ፡፡

ከኢንስቲትዩቱ ፈቃድ ያገኙ ተመራማሪዎች የተፈቀደላቸውን የጀነቲክ ሀብት ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ እንዳያውሉ እንዲሁም ለ3ኛ ወገን አሳልፈው እንዳይሰጡ የሚከታተልበት የአሰራር ስርዓት በውሉ መሰረት እየተተገበረ ስለመሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ ተጠይቆ ያላቀረበ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህገወጥ የጀነቲክ ሀብት ዝውውርን ለመቆጣጠር ጠንካራ የህግ የአሰራር መመሪያ ባለመኖሩ ህገወጥ የጀነቲክ ሀብት ዝውውር እየተበራከተ መምጣቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ተናግሯል፡፡

የኢንስቲትዩቱን በህገወጥ መንገድ የሚደረግ የጀነቲክ ሀብት ዝውውርን በተመለከተ ከ2015-2017 በጀት ዓመት ያለዉ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው፤ 35 የሚሆኑ ተቋማት ላይ በተደረገው ቁጥጥርና ክትትል ውስጥ 17ቱ በህገወጥ መንገድ የጀነቲክ ሀብት ዝውውር አድርገዋል፡፡

እነዚህ ተቋማት ላይ ግንዛቤና የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከመጻፍ ውጭ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እየቀጣ አለመሆኑ ተገልጿል፡፡

ቁምነገር አየለ

ሰኔ 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *