የሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን እስራኤል በሊባኖስ ላይ ያደረገችውን ጦርነት ለማቆም የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ሊባኖስ እንደምትቀበል አስታዉቀዋል።
ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ የውስጥ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ገብነትን ሊቀበሉ እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ማንም ለሊባኖስ በመወከል አይደራደርም ሲሉ ያስገነዘቡት አውን፤ የሊባኖስ ህዝብን ለመጠበቅ ኃላፊነቱ የመንግሥት እንጂ የሃይማኖት ቡድኖች እንዳልሆነ ገልጸዋል።
በተመሳሳይ ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር እስራኤል ጥቃቷን እንድታቆም እና በጦርነት የተጎዳውን ደቡብ ሊባኖስ እንድትለቅ ጠይቃለች።
ይህም የኢራን አጋር የሆነውን ሄዝቦላህ ለመደገፍ መሆኑ ተገልጿል።
ትዕግስት ግርማ
ሰኔ 15/2018 ዓ.ም
