በኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር ፈጣን እድገት እያሳየ ቢሆንም የሳይበር ስጋቶች ተግዳሮት መሆናቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የዲጂታል ፋይናንስ ሽግግር በሌሎች አገራት የ25 ዓመታት ጉዞን በአጭር ጊዜ የቀለበሰ መሆኑ ተነግሯል።

ሆኖም ይህ ፈጣን እድገት ከሳይበር ጥቃት እና ከፋይናንስ ማጭበርበር ስጋቶች ጋር መምጣቱ ተመልክቷል።

የብሔራዊ ባንክ የቴክኖሎጂ አማካሪ ዶክተር ናኦል አዲሱ በሁዋዌ የፋይናንስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 24 ቢሊዮን የሚጠጉ የዲጂታል የገንዘብ ዝውውሮች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

ይህ ትልቅ ስኬት ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ኢላማ ከሆኑ አገራት ተርታ መሰለፏን እና የፋይናንስ ተቋማት ለዚህ ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዶክተር ናኦል በንግግራቸው “የዳታ እና የመሠረተ ልማት ሉዓላዊነት” (Data Sovereignty) አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ሰጥተዋል።

አብዛኞቹ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መረጃዎችን ከአፍሪካ ውጭ በሚገኙ የመረጃ ማዕከላት (Data Centers) እንደሚያስቀምጡ ጠቅሰው፣ ይህም በብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁመዋል።

በመሆኑም ወደፊት የሚመጡ ቴክኖሎጂዎች የኅብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ (Utilitarian Innovation) እና የደንበኞችን መብት የሚያስጠብቁ መሆን እንዳለባቸው ተገልጿል።

በጉባኤው ላይ የተሳተፉት የሁዋዌ ተወካዮች በበኩላቸው፣ የፋይናንስ ተቋማት አስተማማኝ እና ዘመናዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት እንዲገነቡ ድጋፋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ልዑል ወልዴ

ሰኔ 17/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *