ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ‹‹ለማህፀን ካንሰር መንስኤ ሆኗል›› ተብሎ የቀረበበትን በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ክሶች ለመፍታት የ5.5 ቢሊየን ዶላር ክፍያ ለመፈጸም ተስማምቷል።
ግዙፉ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ ባወጣው መግለጫ፤ ስምምነቱ በፌዴራል እና በግዛት ፍርድ ቤቶች የሚገኙ 69,000 የሚሆኑ ጉዳዮችን የሚሸፍን ሲሆን፣ ስምምነቱ የሚፀናው በክፍለ ግዛት ወይም በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ካሉ ከሳሾች መካከል 95 በመቶዎቹ ስምምነቱን ሲቀበሉት ብቻ ይሆናል።
የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የሕግ ጉዳዮች ኃላፊ ኤሪክ ሃስ፤ ስምምነቱ ኩባንያው ‹‹ይህን ጉዳይ በሰላም እንዲዘጋው›› ያስችለዋል ብለዋል።
ከሳሾችን የሚወክሉ ጠበቆችም ስምምነቱን ለአሥር ዓመታት ለዘለቀው የፍርድ ቤት ክርክር ጥሩ መፍትሔ ነው በማለት ተቀብለውታል።
በጥቅምት 2025 የቀረበው የእንግሊዙ ክስ፣ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ታልክ የማህፀን ካንሰርን እና ሜሶቴሊዮማን ሊያስከትል እንደሚችል እያወቀ ምርቱን መሸጡን ቀጥሏል ሲል ይከሳል።
ኩባንያው ግን ይህንን ክስ ይክዳል።
ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት በእንግሊዝ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እየታየ ይገኛል።
እስከዳር ግርማ
ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
