የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት 49ኛ መደበኛ ስብሰባውን በአዲስ አበባ በሚገኘው የህብረቱ ዋና መስሪያ ቤት በሁለት ቀናት ውይይት በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል።
የአህጉሩን ውህደት ለማፋጠን፣ ተቋማትን ለማጠናከር እና አጀንዳ 2063ን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊና ፖሊሲያዊ ጉዳዮች ላይ መምከሩ ተገልጻል፡፡
የህብረቱ የበጀት፣ የፋይናንስ፣ የንግድ፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ሪፖርት ተገምግሟል።
ህብረቱ ባወጣው መግለጫ የ2026 ዓ.ም የህብረቱ የውሃና የንፅህና መጠበቂያ መርሃ-ግብር፣ የጂ20 (G20) ተሳትፎ፣ እንዲሁም የፍሪካ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል (Africa CDC) እና የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጀንሲ (AMA) ሪፖርቶች ተመርምረዋል ብሏል።
ቡሩንዲ የ0.2% ታሪፍ መዋጮ ተግባራዊ ለማድረግ በመወሰኗ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ፣ አንጎላ እና ኬንያ ወደ አንደኛ ደረጃ አዋጭ ሀገራት በመቀላቀላቸው አድናቆት እንደተሰጣቸው ተገልጻል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የውጭ ኦዲተሮች ቦርድ አባላት የተሾሙ ሲሆን፣ በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም በግብፅ የሚካሄደውን አጋማሽ ዓመት ቅንጅት ስብሰባ ሰነዶች እና ተያያዥ ውሳኔዎች ፀድቀዋል።
ባጠቃላይ ስብሰባው የአፍሪካ ህብረት ተቋማትን ማጠናከር፣ በአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የአፍሪካን አንድነት ማጎልበት እና አጀንዳ 2063ን ማፋጠን እንደሚገባ አጽንኦት እንደተሰጠበት ታውቋል፡፡
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
