የዮጋ መምህሩ በአንድ ትንፋሽ 86 ፑሽ አፖችን በውሃ ውስጥ በመሥራት አዲስ የዓለም ሪኮርድ አስመዘገበ

​በቪየትናም የሚኖሩት የ38 ዓመቱ የዮጋ መምህር ካማል ካሎይ በአንድ ትንፋሽ ብቻ 86 ፑሽ አፖችን በውሃ ውስጥ በመሥራት አዲስ የጊነስ ዓለም ሪኮርድ ማስመዝገባቸው ተረጋገጠ።

 ትውልደ ህንዳዊው ካማል ካሎይ በኒን ቢን በሚገኝ የመዋኛ ገንዳ ውስጥ ያደረጉትን አስደናቂ ሙከራ የጊነስ ዓለም ሪኮርድ ተቆጣጣሪዎች መርምረው በማፅደቅ በአንድ ትንፋሽ በውሃ ውስጥ በጣም ብዙ ፑሽ አፕ የሠራ ወንድ በማለት ታሪካዊ ስኬታቸው እውቅና ተሰቶታል።

​ለዚህ ስኬት ያበቃቸው በ’’ካሊስቴኒክስ’’ ወይም የሰውነት ጥንካሬ እንቅስቃሴ እና በዮጋ ያካበቱት የትንፋሽ ቁጥጥር ልምድ እንደሆነ የተናገሩት ካማል፣ ከጥንት ጀምሮ የተለየ ነገር የማድረግ ፍላጎት እንደነበራቸው ገልጸዋል።

አክለውም ሌሎች ሪኮርድ ያስመዘገቡ ሰዎችን ባዩ ቁጥር ይነሳሱ እንደነበርና የመጀመሪያውን የውሃ ውስጥ ዮጋ የዓለም ሪኮርድ በሠሩበት ወቅት አቅማቸውን ተረድተው ራሳቸውን የበለጠ ለመፈታተን እንደወሰኑ አስረድተዋል።

​ይህ ለካማል ካሎይ የመጀመሪያው የዓለም ሪኮርድ አይደለም። እ.ኤ.አ. በ2020 በውሃ ውስጥ 21 ተከታታይ የዮጋ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ የመጀመሪያውን የጊነስ ዓለም ሪኮርድ ይዘው የነበረ ሲሆን፣ ዮጋ ትንፋሽን በውሃ ውስጥ እስከ ስድስት ደቂቃ ያህል ለመያዝ እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገላቸው ገልጸዋል።

ሐመረ ፍሬው

ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *