የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀነሬሽን ቢዝነስ ዘርፍ እንዳስታወቀው፤ በ2018 በጀት ዓመት ከ35 ሺህ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማመንጨት ተችሏል።
የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ወልደኪዳን እንዳሉት፤ በበጀት ዓመቱ 38 ሺህ 124 ነጥብ 78 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማምረት ታቅዶ ነበር። የተመረተው 35 ሺህ 670 ነጥብ 99 ጊጋ ዋት ሰዓት ሲሆን፤ ይህም የዕቅዱን 93 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት መቻሉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
ይህ አፈጻጸም ከ2017 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ21 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።
ኢንጂነር ኤፍሬም አክለው እንዳብራሩት፤ ከተመረተው ጠቅላላ ኃይል ውስጥ፡ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ማለትም 51 ነጥብ 5 በመቶውን ያመነጨው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 17 ነጥብ 8 በመቶ፣ እንዲሁም የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 7 በመቶ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸው ተናግረዋል።”
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበጀት ዓመቱ ከ35 ሺህ ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኤሌክትሪክ ማመንጨቱን አስታወቀ
