የኢራን ቀይ መስቀል ማህበር እንዳስታወቀው፣ በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ የሰርግ ስነ-ሰርዓት ላይ በአሜሪካ ጥቃት ምክንያተት አራት ሰዎች (አንድ ህጻን ጨምሮ) ህይወታቸው አልፏል፤ ከ50 በላይ ሰዎችም ቆስለዋል።
ቀይ መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው ጽሁፍ፤ “በአሜሪካ የሚሳኤል ጥቃት የቦምብ ፍንጣሪ በሆርሞዝጋን ግዛት በሲሪክ ወረዳ ኩሄስታክ ከተማ የሰርግ ዝግጅት እየተካሄደበት በነበረ የመኖሪያ ቤት ላይ አርፎ የሰዎችን ህይወት አጥፍቱዋል” ብሏል።
ማህበሩ አክሎም “ከ50 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፤ አንድን ህጻን ጨምሮ አራት ሰዎችም ሰማዕትነት ተቀብለዋል” ሲል ገልጿል።
የኢራን የመንግስት ይፋ ያደረገው ቪዲዮ፣ በሲሪክ በሚገኘው የሰርግ ስፍራ ላይ የደረሰውን ሰፊ ፍርስራሽ እና ጉዳት የሚያሳይ ሲሆን፣ በስተጀርባም የሰዎችን ድምጽና ጩኸት ማድመጥም ተችሏል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እስካሁን ድረስ ስለተባለው ድርጊት መረጋገጥ የሰጡት አስተያየት የለም፤ነገር ግን ኢራን ለደረሰው ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ እንደምትሰጥ ዝታለች፡፡
በደቡባዊቷ ሲሪክ ወረዳ የምትገኘው ስፍራ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ባለው የሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ ትገኛለች።
ሀና ሰይፉ
ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም
