የዘንድሮው የጳጉሜ ወር“የኢትዮጵያ ማንሰራራት” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቅ ድምቀት ይከበራል ተባለ።

​የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት  በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ፥ በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ ታሪካዊ ሀገራዊ ስኬቶችን መነሻ በማድረግ አምስቱም የጳጉሜ ቀናት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ከፍታ በሚያሳዩ አምስት መርሃ ግብሮች እንደሚከበሩ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት የግብርና ምርታማነት ማደጉ፣ የገቢ አሰባሰብ ከ1.5 ትሪሊየን ብር መሻገሩ እና ከውጭ ንግድ 10.2 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ ተጠቃሽ ምክንያቶች በመሆን ጳጉሜ 1 “የእመርታ” ቀን ተብሎ ይከበራል።

ሀገሪቱ ከጎታች ማነቆዎች ተላቃ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሳየት የጀመረችበት እና ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ዲጂታል ኢኮኖሚ የዕድገት ምሰሶዎች መሆናቸውን ያረጋገጠችበት አመት በመሆኑ ደግሞ ጳጉሜ 2 “የማንሰራራት” ቀን በመባል ተሰይሟል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያጸኑ ጀግኖች የሚዘከሩበትና በሁሉም ተቋማት የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ሥነ-ሥርዓት የሚከናወንበት ጳጉሜ 3 “የጽናት ቀን” ተብሎ ሲከበር፥ ለ1መቶ50 ሺህ ወገኖች ነፃ የጤና ምርመራ እና የበጎ አድራጎት ሥራዎች የሚከናወኑበት ጳጉሜ 4 ደግሞ “የኅብር ቀን” ተብሏል።

የመጨረሻው የጳጉሜ ዕለት “ኢትዮጵያ ነገን ዛሬ ላይ እየሠራች ነው” በሚል መሪ ሐሳብ የዲጂታል ኢኮኖሚ አቅምን መጠቀም እና ወጣቶችን በክህሎት ማብቃት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ጳጉሜ 5 “የነገ ቀን” በመባል እንደሚከበር አገልግሎቱ በመግለጫው አስታውቋል።

ሐመረ ፍሬው

ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *