የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት እና የማጠቃለያ መርሃ ግብር ሀሙስ መስከረም 9/2017 ዓ.ም በድሬደዋ ከተማ ይደረጋል።
በእለቱ በ7 ዘርፍ የአመቱ ኮከቦች ይሸለማሉ ፤ ለተሳታፊ ክለቦች እና ባለሜዳዎች የገንዘብ ክፍፍል ይደረጋል።
መርሃ ግብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ውጪ የ2017 ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሚጀመርባት የበረሀዋ ንግስት ድሬደዋ የሚደረግ ይሆናል።
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም
