በቅርቡ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትነት ስራቸው የለቀቁት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል፡፡
ሹመቱ ከዛሬ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተሠጠ መሆኑን ባንኩ አሳውቋል።
ፕሬዝዳንቱ ስራቸውን የለቀቁት “በፈቃዳቸውና በግል ምክንያት” መሆኑን መናገራቸው የሚታወስ ነው ።
በስራ ዘመናቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከነበረበት ውስብስብ ችግርና ክስረት ወደ ተሻለ አቋም እንዲመለስ ማስቻላቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች ይመሰክሩላቸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም
