“አሁንም ከመንግስት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነን “ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አሁንም ከመንግስት ጋር ለመስራት ዝግጁ ነው፣ ነገር ግን ምን አይነት የሀላፊነት ቦታ ላይ እንደምንመደብ ቀድሞ ሊነገረን ይገባል ሲሉ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር አብዱልቃድር አደም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል። በዛሬው ዕለት በተካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር […]

“የተሾምኩበት በትክክለኛው ቦታ ነው፣ከዚህ ሃላፊነት ውጪ ቢሰጠኝ ኖሮ አልቀበልም ነበር” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የሚንስትሮች ሹመት የትምህርት ሚንስትር ሆነው የተሾሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የተሾምኩበት በትክክለኛው ቦታ ነው፣ከዚህ ሃላፊነት ውጪ ቢሰጠኝ ኖሮ አልቀበልም ነበር ብለዋል፡፡ ይህንን ሃላፊነት እንደማገልገል ከወሰድነው ከዚህ መስሪያ ቤት ውጪ ሌላ ሃላፊነት ቢሰጠኝ አልወስድም ነበር፡፡ ትምህርት በፍቅር የሚሰራ ስራ ነው፡፡የትምህርት ሚንስቴርም ትልቅ ተቋም ነው የተሰጠኝም ሃላፊነት ትልቅ ሹመት ነው በማለት ተናግረዋል፡፡ […]

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በስራ አስፈጻሚነት ደረጃ ያቀረቧው እጩዎች

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ዑመር ሁሴን – ግብርና ሚኒስቴር አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገብረ መስቀል ጫላ – የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ – የጤና ሚኒስቴር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ – የቱሪዝም ሚኒስቴር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል – የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አቶ አህመድ ሽዴ – የገንዘብ ሚኒስቴር አቶ ላቀ አያሌው – የገቢዎች ሚኒስቴር […]

6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት ከተነሱ ጉዳዮች መካከል

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

• ክልሎች የፀጥታ ችግር ሲገጥማቸዉ የፌደራሉ መንግስት በፍጥነት ኃይል በማሰማራት የማረጋጋት ስራ መስራት አለበት ለዚህ ደግሞ እራሱን የቻለ በማእከል ደረጃ ኮማንድ ሊቋቋም ይገባል፡ • የፀረ ሙስና ኮሚሽ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት መሆኑ ግልፀኝነትን አያረጋግጥም፡፡ • በርካታ አንገብጋቢ አገራዊ ጉዳዮች ባሉበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 20 የሚሆኑ የፌደራል መስሪያ ቤቶችን እንዲቆጣጠሩ ስልጣን መሰጠቱ አግባብ አይደለም ተብሏል፡፡ • […]

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ ላይ 22 ሚኒሲቴር መስሪያ ቤቶች ቀርበዋል ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ግብርና ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የማዕድን ሚኒስቴር የቱሪዝም ሚኒስቴር የስራና ክህሎት ሚኒስቴር የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢዎች ሚኒስቴር የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር የጤና ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መከላከያ ሚኒስቴር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር […]

የጉሙዝ ታጣቂዎች በሴዳል ወረዳ 145 ሰዎች ማገታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከልና ካማሺ ዞኖች የዜጎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ መፍጠን እንዳለበት አሳሳበ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ኢሰመኮ በቤኒንሻንጉል ካማሺ ዞን የሚገኘው የሴዳል ወረዳ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጾ፣ በክልሉ መተከል እና ካማሺ ዞኖች ያለውን የፀጥታ ሁኔታና የነዋሪዎችን ደኅንነት ለማረጋገጥ በፌዴራል መንግስቱና በአካባቢው ኮማንድ ፖስት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች በተሻለ ፍጥነት ሊተገበሩና ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስቧል። በተለይም በአሁኑ ወቅት ከሴዳል ወረዳ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሸሽተው የሚገኙ ነዋሪዎች እንደሚገልጹት፣ ከጥር ወር […]

የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ ካቀረቧቸው እጩዎች መካከል አቶ ጣሂር ሙሃመድ ይገኙበታል።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ጣሂር ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች መካከል ሲሆኑ በአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮን በኃላፊነት እንዲመሩ ነው የቀረቡት። ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያንመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ አማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ አስረስ የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በተለያዩ ትምህርት ኮሌጆች በመምህርነት፣ ዲን በመሆንና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንትና ፕሬዝዳንት በመሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያውያንመስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም

የልብ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ከ7 ሺህ በላይ ህጻናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ ሰማን

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የልብ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ከ7ሺህ በላይ ህጻናት ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የሰማነው ከልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ነው፡፡ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማእከል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ህሩይ አሊ በየአመቱ እስከ 500 የሚደርሱ ህጻናት የልብ ቀዶ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ እና ቀዶ ህክምና የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር በየቀኑ እንደሚጨምር ኢትዮ ኤፍ ኤም ከሃላፊው ሰምቷል፡፡ ይህ […]

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በአሁን ሰአት የከተማ አስተዳደሩን አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው 101 አንቀፆች ባሉት ረቂቅ አዋጅ ላይ እየተወያየ ነው፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በረቂቅ አዋጁ መሰረት ካለፈው ምክር ቤት 61 የነበሩት አጠቃላይ የአስፈፃሚ አካላት በአዲሱ ምክር ቤት 46 ሆኖ ሲቀርብ፣ የካቢኔ አባላት ደግሞ 24 እና በከንቲባ እንደ አስፈላጊነታቸው የሚሰየሙ ሌሎች ተቋማትን ጨምሮ አዳዲስ የካቢኔ አባላት የሆኑ ተቋማትን መያዙን ፋና ዘግቧል፡፡ በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት መልሶ ለማደራጀት በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ በካቢኔ ደረጃ የተደራጁ ተቋማት […]