በኢትዮጵያ ተጨማሪ 73 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,844 የላብራቶሪ ምርመራ ሰባ ሶስት (73) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ስድስት መቶ ሃምሳ አምስት (655) ደርሷል፡፡የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦ • የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው – 27 • በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው – 15 […]

የኦስትሪያው ፕሬዝዳንት በአገራቸው የተጣለዉን የሰዓት እላፊ ገደብ ተላልፈዉ በመገኘታቸዉ ይቅርታ ጠየቁ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በሚል በሀገሪቱ ዋና ከተማ ቬይና ካፌዎችና ሬስቶራንቶች ተዘግተዉ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን ስራዎቻቸዉን የሚያከናዉኑባቸዉ ሰዓታት ተገድቦ ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ በተለይም የቁርስና ምሳ ሰዓት አካባቢ ስራዎቻቸዉን ሰርተዉ ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ ዝግ እንዲያደርጉ ይጠቁማል፡፡ የ76 ዓመቱ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ቫን ዲር ቤሌን ግን ከባለቤታቸዉና ከ2 ጓደኞቻቸዉ ጋር በመሆን ከተቀመጠዉ የሰዓት ገደብ በላይ በአንድ […]

የቻይና ኩባንያ ጭምብል ያደረጉ ሰዎችን ማንነት የሚለይ ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የቻይና ኩባንያ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ያደረጉ ሰዎች ማንነት መለየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ይፋ አድርጓል። ቴክኖሎጂው ዓለምን እያስጨነቀ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ለመዋጋት እገዛ እንደሚያደርግ ታምኖበታል። ሃንቮን በተባለው ኩባንያ የተዋወቀው ቴክኖሎጂ ሰዎችን ጭምብል ሳያወልቁ ማንነታቸውን መለየት የሚያስችል ነው ተብሏል። በተጨማሪም ከሰውነት ሙቀት መለኪያ መሳሪያዎች ጋር ከተገናኘ በኋላ ከ38 ዲግሪ ሴሊሺየስ በላይ የሰውነት ሙቀት ያላቸውን […]

ለከፍተኛ ትምህርት በሚል ወደ ሕንድ ያቀኑ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በህንድ የሚማሩ ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች በከፍተኛ የገንዘብ ችግር ዉስጥ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ያሉበትን ሁኔታ ሲናገሩ፣የምግብ መግዣም ሆነ ከሳኒታይዘር ጀምሮ ኮሮናን ለመከላከል የሚያስፈልጉ የህክምና ቁሳቁሶች መግዣ ሳይቀር መቸገራቸዉን ተናግረዋል፡፡ ተማሪ ብሩክና ተማሪ ሃጎስ በስተዲ-ኢን-ኢንድያ ለትምህርት እድል አግኝተዉ ወደ ህንድ ሲያቀኑ በመጀመሪያ ሁሉም ወጫቸዉ እንደሚሸፈንና የኪስ ገንዘብም እንደሚሰጡ ተነግሯቸዉ እንደነበር ያነሳሉ፡፡ ከሄዱ በኋላ የኪስ ገንዘብ […]

ጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ በኢትዮጽያ የተጠለሉ የሶሪያ ስደተኞችን ጎበኙ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ ዛሬ በፌስቡክ ገጻቸው እንዳሰፈሩት የረመዳን ጾም ከማብቃቱ በፊት መልካም የዒድ በዓል እንዲሆንላቸው በመመኘት ዛሬ ሶርያውያን ስደተኞችን ጎብኝቻለሁ። ሶርያውያኑ አስከፊውን ግጭት በማምለጥ መኖሪያቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ ሲሆን፣ የረመዳንን ማብቂያ በክብር ማሳለፍ ይገባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስደተኞች ከሚቀበሉ ሀገራት መካከል እንደ ሆነች ይታወቃል። ሀገራችን በጦርነት ምክንያት ኑሯቸው ለተናጋባቸው ሰዎች ከለላ […]

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የጤናጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 3645 ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አራትመቶሀያ ዘጠኝ(429) ደርሷል፡፡ ግንቦት14 ቀን 2012 ዓ.ም

የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አራት አዲስ ሹመቶችን በማጽደቅ አጠናቀቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በትናንትናዉ ዕለት የ12 የምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት ያነሳውየሶማሌ ክልል ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ረፋድ አጠናቋል። ምክርቤቱ በዛሬው እለት አዳዲስ ሹመቶችን ያፀደቀ ሲሆን1.ዶ/ር ሁሴን አብዱላሂ ቃሲም/ የፀጥታ ቢሮ ሃላፊ 2.አቶ አሊ በደን አደን ማህመድ/ ኮምዪኔኬሽን ቢሮ ሃላፊ 3.አቶ አብዲቃድር ረሽድ /የፐብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ 4. አቶ አብዲ ማህመድ / የማእድን እና […]

ጄም-ኮርፕ የኢትዮጵያ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን 200 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ያወጣውን ጨረታ በድጋሚ ማሸነፉን አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጄም-ኮርፕ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ 200 ሺ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለብሔራዊ የአደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚሽን መሥሪያ ቤት ለማቅረብ ለተጨማሪ ዙር ጨረታውን ማሸነፉን አስታውቋል፡፡ በኢትዮጵያ የጄም-ኮርፕ ተቋም ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ኮስታስ ላለፉት 18 ወራት ጄምኮርፕ ጠንካራ እና አስተማማኝ የግብርና ምርቶች ንግድ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመዘርጋት በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በአሁን ሰዓትም ፉርኖ ዱቄት እና […]

ግብፅ በድጋሚ ወደ ህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ስለመመለስ ለኢትዮጵያ በይፋ ያሳወቀችው ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ግብጽ ከኢትዮጵያ እና ሱዳን ጋር ለመወያየት ወደ ዳግም ውይይት ለመመለስ መወሰኗን በውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ በኩል ማሳወቋን ዴይሊ ኒውስ ኢጅፕት የተሰኘው የግብጽ መገናኛ ብዙሀን ዘግቧል። የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደገለፀው ግብፅ በድጋሚ ወደ ድርድሩ ለመመለስ የወሰነችው ኢትዮጵያ የአቋም ለውጥ አድርጋ አይደለም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አቶ አምሳሉ ትዛዙ ለጣቢያችን እንደተናገሩት እኛም እንደናንተ […]

ዛሬ ምሽት ቡንደስሊጋ ሄርታ በርሊን ከ ኡኒየን በርሊን ያገናኛል።

Posted Leave a commentPosted in ስፖርት

ሁለቱ ክለቦች የምስራቅ እና ምዕራብ በርሊን ተወካዮች ናቸው ። በሁለቱ ቡድኖች መካከል ባለፈው ህዳር የተደረገው ጨዋታ የማይረሳ ነው። ደጋፊዎች ተቀጣጣይ ነገሮችን ወደ ሜዳ በመወርወራቸው ጨዋታው ለደቂቃዎች ተቋርጦ ነበር። ኡኒየን በርሊን የማሸነፊያዋን ጎል ያስቆጠረው መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቅቆ በተጨመረው የባከነ ሰዓት 10ኛው ደቂቃ ላይ ነው። ዛሬ በኦልምፒክ ስታዲየም ከሄርታ በርሊን ጋር የሚደረገው ጨዋታ በኮሮና ቫይረስ […]